የሁልባራግ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

የሁልባራግ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ ዲዛይን

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም ከፍተኛና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም ከፍተኛና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

የፓርቲ ሥራዎች ድጋፍና ክትትል

የ2018 ዓ.ም የፓርቲ ሥራዎችን በመገምገም፣ ጥንካሬዎችን ለማጠናከርና ክፍተቶችን ለመለየት የድጋፍና ክትትል ሥራ ተካሂዷል።

ኮሪደር ልማት ኢንሼቲቭ

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢኒሼቲቭ የተገነባ የገጠር ኮሪደር ልማት በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ

ክቡር አቶ አደም ፋራህ

"የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ በመገኘት የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተመለከቱ።"

የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሙላጎ ከይረዲን መልዕክት

Mulago KehredinAbdelaሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ውብ ተምሳሌት የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። የተለያዩ ማንነቶች፣ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች በአንድነት የደመቁባት ሀገራችን፣ ልዩነቷን ወደ ጥንካሬና ውበት በመቀየር ለዘመናት በመከባበርና በመቻቻል የኖረች ናት። ዜጎቿም ውድ ሕይወታቸውን በመስዋዕትነት በመክፈል የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረው ለትውልድ አስረክበዋል።

ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠሩ የተዛቡ ትረካዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች ይህንን የጋራ እውነታችንን ለመሸርሸር ሞክረዋል። አንዳንድ ኃይሎችም አባቶቻችን የሀገር ምሰሶ ያደረጓቸውን እሴቶች የጥንካሬ ምንጭ ሳይሆን የድክመት ምንጭ ለማድረግ ሲሰሩ ቆይተዋል።የሀገራዊ ለውጡ ፈንጣቂ የሆነው የብልፅግና ፓርቲ ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በዘላቂነት መፈወስ የሚቻለው በአገራዊ አንድነት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። ለዚህም ነው አገራዊ አንድነታችንን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ የትኩረታችን ማዕከል ያደረግነው።

 በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በወረዳዋ ነዋሪዎች የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። የሁልባራግ ወረዳ የሰላም፣ የአንድነትና የልማት ማዕከል እንደመሆኗ፣ በተለያዩ ዘርፎች የሚመዘገቡ ውጤቶች የወረዳዋን ብሎም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የሚያበረክቱ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በሁልባራግ ወረዳ የሰላምና የመረጋጋት አየር በማጠናከር፣ የወረዳ ልማትን በማስፋፋት፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማሳደግ እንዲሁም የሕዝብና የመንግስት ትስስርን በማጠናከር የሚታዩ ውጤቶችን አስመዝግበናል። የሁልባራግ ወረዳ የብልፅግና አሻራም በተጨባጭ እየጎላ መጥቷል። እርግጥ ነው፣ በጉዟችን ላይ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ሆኖም እኛ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ፣ አቅማችንን ወደ ላቀ ውጤት፣ ተግዳሮቶችንም ወደ ታላቅ ስኬት በመቀየር፣ በመተሳሰብና በወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ውድ የሆነችውን ሁልባራግ ወረዳን፣ የስልጤን ሕዝብና ታላቋን ኢትዮጵያ ከፍ ለማድረግ በፅናት ወደፊት ተጉዘናል፤ ጉዟችንንም እንቀጥላለን! በሁልባራግ ወረዳ በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መላው የወረዳችን ማህበረሰብ፤ የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር፣ ድህነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ሙስናን በቆራጥነት በመታገል፣ የድካማችን ማማና የልፋታችን ውጤት የሆነውን ሁሉን አቀፍ ብልፅግና ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ትጋትና በተቀናጀ ተሳትፎ ነው። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የሁልባራግ ወረዳ ነዋሪዎች እንደ ሁልጊዜው የጽናታችን አለኝታና የጉዟችን ደጋፊ ሆናችሁ ከጎናችን እንደምትቆሙ ሙሉ እምነት አለን። በመጨረሻም፣ ለዴሞክራሲያችን መጎልበት የማይተካ ሚና ያላችሁ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለሁልባራግ ወረዳ፣ ለስልጤ ሕዝብና ለታላቋ ኢትዮጵያ ብልፅግና ሲባል በትብብርና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ ፍቅርና ልፋት ትበለፅጋለች! 

                                                                                                            አመሰግናለሁ!"

አምልጦዎት ይሆን |You May Have Missed

 

ሚዲያ እና ገጽ| Our Media

አጋሮቻችን I Our Partner