የሁልባራግ ወረዳ አስተዳደር ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን እየገመገመ ይገኛል።
ሐምሌ 21/2018
በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ አስተዳደር ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በሳምንታዊ መድረክ እየገመገመ ይገኛል።
መድረኩን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፋ ሀምዳላ እና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙላጎ ከይረዲን አየመሩት ሲሆን ቀበሌያት የወቅታዊ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛል።
በመድረኩ ወቅታዊ የግብርና ተግባራት፣ የገጠርና የከተማ ኮሪደር፣ ተረጂነት፣ የመከላከያ ተግባር፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የህብረቶች ኮንፍራንስ አፈፃፀም፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የጤና ተግባራት፣ የገቢ ስራና ሌሎች ወቅታዊ ተግባራት በዝርዝር እየተገመገሙ ይገኛል።
በመድረኩ የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪዎች አቶ ሙሰማ ሽፋና አቶ ኑረዲን መሀመድን ጨምሮ የወረዳ አጠቃላይ አመራሮችና የቀበሌ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።